#Fastmereja I3ተኛዉ የጆርካ 43ተኛዉ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1ኛ እና የ2ኛ ዲቪዚዮን ውድድር ሊካሄድ መሆኑ በዛሬዉ እለት ተገልጿል።
መርሀ-ግብሩ ከነገ መጋቢት 02 እስከ መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በአደይ አበባ ስታዲየም ነዉ የሚካሄደዉ።
በአደይ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የበርካታ ክለቦች አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
ለዚህ ዉድድር 2 ሚሊየን ብር ለአትሌቶችና ለአሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት በጆርካ ኤቨንት የተሸፈነ ሲሆን 1ኛ ለወጣ 3000 ብር ለ2ኛ 2000 ብር እንዲሁም 3ኛ ለውጣ 1000 ብር ሽልማት መዘጋጀቱም በመግለጫዉ ተገልጿል።
በነገዉ እለት በሚጀመረዉ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የውድድሩ ዓይነቶች ርዝመት ዝላይ፣ አሎሎ ውርወራ ፣ 10,000 ሜትር ፣ 100 ሜትር መሰናከል ፣ 110 ሜትር መሰናከል ፣ 100 ሜትር ፣ 400 ሜትር ፣ ምርኩዝ ዝላይ ፣ ዲስከስ ውርወራ ፣ 1500 ሜትር ሩጫ ፣ ከፍታ ዝላይ ፣ 5000 ሜትር ፣ 800 ሜትር ፣ እርምጃ ፣ ጦር ውርወራ ፣ ስሉስ ዝላይ ፣ 200 ሜትር ፣3000 ሜትር መሰናከልና መዶሻ ውርወራ መሆናቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።




