banner

ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ለ46ተኛ ዙር ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች አስመረቀ!

#FastMereja I ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ለ46ተኛ ዙር በተለያዩ የዉበት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ከ50በላይ ተማሪዎችን ቦሌ በሚገኘዉ ሳማራ ሆቴል በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል።

በሜካፕ፣ በጥፍር፣ በጸጉር በአይላሽ ሽፋሽፍት የውበት ሞያ ዘርፎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነዉ ያስመረቀዉ።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የዲጂታል እና የመደበኛ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች፣ በውበት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች/የድርጅት ባለቤቶች እና የተማሪዎች ወዳጅ ዘመዶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋምዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የውበት ትምህርት ለማድረስ ካለው ቁርጠኛነትና ትጋት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እና ከፍለው መማር የማይችሉ ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት የሞያ ባለቤት በማድረግ ብሩህ ተስፋ ያላቸውና የፋይናንስ ነጻነት ያላቸው አምራች ዜጎች እንዲሆኑ እድሎችን በማመቻቸት ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ስመጥር ድርጅት ነው፡፡

ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ማሰልጠኛ ተቋም ከተለያዩ የአውሮፓ ተቋማት ጋር የሀገራችን የውበት ኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሳደግ እና ለተማሪዎች የስራ እድሎችን ለማስፋት በስፋት እየሰራም የሚገኝ ሲሆን በአሁን ወቅት ተደራሽነቱን በማስፋት በካናዳ በተለያዩ እስቴቶች በርካታ ተማሪዎችን አሰልጥና ያስመረቀች ሲሆን አሁንም በማስተማር ላይ ትገኛለች።

#ልዩ_ልዩ





Leave a Comment