banner

“ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እናቴ አልተኝም በቤቴ!” በሚል የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥ

“ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እናቴ አልተኝም በቤቴ!” በሚል የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ሥርጭት መርሃ ግብር ተዘጋጀ

#FastMereja I በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር ከሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ የሆነው የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም፣ ለጀመረው ባለ ሁለት ቤተ መቅደስና ባለ ስድስት ወለል ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚውል “ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እናቴ አልተኝም በቤቴ!” በማለት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ገዳሙ እንደገለጸው፣ ይህ ግዙፍ ሁለገብ ሕንፃ በ1200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እያረፈ ያለ ሲሆን፤ ግንባታው ያስፈለገባቸው ምክንያቶች፦ የአሁኑ የክርስትና ማጥመቂያ ቦታ ጠባብ በመሆኑ ሰፊ የክርስትና ማጥመቂያ አዳራሽ ለመገንባት። ለሰርግ፣ ለጉባኤና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል አዳራሽ ለማዘጋጀት። ለአባቶች ማረፊያ፣ ለገዳሙ አስተዳደር ቢሮዎች እና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ነው።

የሕንፃው አጠቃላይ የግንባታ ወጪ 640 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ የተገመተ ሲሆን፣ እስካሁን በምዕመናን ድጋፍ 135 ሚሊዮን ብር (20%) የሚገመት ሥራ ተከናውኗል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በገንዘብ እጥረት ምክንያት የግንባታው ሂደት ተቋርጦ ይገኛል።

የቀሩትን 80% የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅና ሕንፃውን በ2019 ዓ.ም ለመመረቅ እንዲቻል፣ ገዳሙ የሚከተለውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፦

📍ከመጋቢት 11 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍በየቀኑ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ
📍በሚዲያ ቴክኖሎጂ የታገዘ የቀጥታ (Live) ሥርጭት

ምዕመናንና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ የገዳሙ ወዳጆች በሚከተሉት የባንክ አካውንቶችና ስልኮች በመጠቀም አሻራችሁን እንድታርፉ ጥሪ ቀርቧል፦

የባንክ አካውንቶች፦
📌 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000003780779
📌 ኦሮሚያ ባንክ፦ 0088911720301
📌 አቢሲኒያ ባንክ፡- 9841011002322017

ለበለጠ መረጃና ቃል ለመግባት፦
• 0911-19-05-03 / 0911-59-26-05
• 0911-44-61-44 / 0957-66-39-39

መርሐግብሩን ለበርካታ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሓግብር በማዘጋጀት የሚታወቀው ሎዛ ኩነቶች ሲሆን ገዳሙ በማጠቃለያው “ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እናቴ አልተኝም በቤቴ!” በሚል መሪ ቃል፣ ሁሉም የኪዳነ ምሕረት ልጆች ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።





Leave a Comment