0
#FastMereja I በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ “ቀፊራ ብረታብረት” ተብሎ በሚጠራው ሰፈር፣ አስገራሚና ብርቅዬ ተፈጥሯዊ ክስተት ተሰማ። በአካባቢው የሚገኝ ግለሰብ ንብረት የሆነች ፍየል፤ ስምንት እግር፣ አራት ጆሮ እና ሁለት የሴት ጾታ ብልት ያላት ግልገል መውለዷ ነዋሪውን አስገርሟል።
የፍየሏ ባለቤት አቶ ኤፍሬም ተሾመ እንደገለጹት፤ እናቲቱ ፍየል ለመጀመሪያ ጊዜ የወለደች (አውራጅ) መሆኗን ጠቅሰው፣ ለረጅም ዓመታት በርካታ ፍየሎችን ቢያረቡም እንዲህ ያለ አጋጣሚ ገጥሟቸው እንደማያውቅ በግርምት ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የተወለደችው ግልገል በገጠማት የአካል መዛባት ምክንያት በሕይወት መቆየት አልቻለችም። እናቲቱን ፍየል ከሞት ለመታደግ ሲባል ግልገሏ ልትሞት እንደቻለች ባለቤቱ የገለጹ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት እናቲቱ ፍየል በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል።
ይህ ክስተት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። በተፈጥሮ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ እንዲህ ያሉ ክስተቶች ለእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎችና ለተመራማሪዎች ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው።
ዘገባው የመናኸሪያ ሬዲዮ ነው።
#ልዩ_ልዩ
