banner

በደቡብ ኢትዮጵያ በደረሰው አደጋ ምክንያት የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

​#FastMereja I የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን፣ በጋጮ ባባ ወረዳ፣ ላካ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን አወጀ።

​መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው በዚህ አሰቃቂ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ ከ125 በላይ ሰዎች ለጉዳት የተዳረጉ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ የ80 ወገኖች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። የተቀሩት ደግሞ በከባድ ፍለጋ ላይ ይገኛሉ።

​ምክር ቤቱ ከአዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ከነገ መጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን እንዲሆን ወስኗል።

​በእነዚህ የሐዘን ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል።

Leave a Comment