0
#FastMereja I የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት ከኢፌዴሪ መንግስት እና ህዝብ ጎን መሆኗን ገልጻለች።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (MoFA) ባወጣው መግለጫ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እንዲሁም ለኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝቷል።
ሀገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት እና አጋዥነት አረጋግጣለች። በአደጋው ለተጎዱት ሁሉ አፋጣኝ ማገገምን እና ለሟች ቤተሰቦች ጥንካሬን ተመኝተዋል።
