#FastMereja I የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የዲጂታል መድረኮች ላይ ህዝብን የሚያሳስቱ እና የተቀነባበሩ የቪዲዮ ምስሎችን በመልቀቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 10 ተከሳሾች እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሲሆኑ 2 ህንዳውያን፣ 1 ፓኪስታናዊ፣ 1 ፊሊፒንሳዊት፣ 1 ግብፃዊ፣ 1 ባንግላዴሻዊ፣ 1 ካሜሩናዊ፣ 1 ኔፓላዊ፣ 1 ቪየትናማዊ እና 1 ኢራናዊ ናቸው።
ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ ያሰራጯቸው ቪዲዮዎች፦ እውነተኛ እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተቀነባበሩ ምስሎችን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የቦምብ ፍንዳታዎች፣ ጥቃቶች እና የደህንነት ስጋቶች እንዳሉ የሚያሳዩ የሃሰት መረጃዎች ናቸው።
ምርመራው እንደሚያሳየው፣ የቪዲዮዎቹ ዋና ዓላማ ህዝቡን ማሳሳት እና ፍርሃትን መርጨት ነው።
ተከሳሾቹ በአፋጣኝ ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል።
እንዲህ ያሉ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር መሆኑን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በህጉ መሰረት ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ግለሰቦች ቢያንስ የአንድ ዓመት እስራት እና ከ 100,000 ድርሃም (AED) ጀምሮ የሚቀጣ የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል።
