0
#FastMereja I በቲክቶክ መንደር ሰሞኑን የብዙዎችን ቀልብ የሳበ አንድ ድንቅ ጥንድ ታይቷል። አንዱ “ወፍራሙ” ሌላዋ “ቀጭኗ” እየተባሉ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ የሆኑት ግዛቸው እና አመርቲ፣ ፍቅር በቁጥር እና በክብደት እንደማይለካ በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
ግዛቸው ገና የ22 ዓመት ወጣት ቢሆንም፣ የ175 ኪሎ ግራም ግርማ ሞገስ አለው። በሌላ በኩል ደግሞ የ20 ዓመቷ አመርቲ የ34 ኪሎ ግራም ክብደት ያላት ጭምት ወጣት ናት። እነዚህ ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ውበቶች ሰሞኑን “ገመዳ ሾው” ላይ ቀርበው የልባቸውን አውግተዋል።
በቆይታቸውም የሰጡት ምላሽ የብዙዎችን ልብ ነክቷል። በመካከላቸው ያለው የክብደት ልዩነትም ሆነ የሰዎች አስተያየት ሳይገታቸው፣ ወደ ፊት በትዳር ተሳስረው አብሮ ለመኖር ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው በግልጽ ተናግረዋል።
ይህ ታሪክ ፍቅር መልክ፣ ቁመትና ክብደት ሳይሆን ንጹህ ልብና መግባባት መሆኑን ዳግም ያስመሰከረ ሆኗል። ለወጣቶቹ መልካም የፍቅር ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን!
#ልዩ_ልዩ
