0
#FastMereja I መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.
በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማራው 888 Software System LLC በኢትዮጵያ ወንጀል መስራት ቀርቶ፣ ወንጀልን ማሰብ እንኳን እንዳይቻል የሚያደርግ አዲስ ፕሮጀክት ማጠናቀቁን አስታወቀ። የድርጅቱ ባለቤት አቶ ወልደጊዮርጊስ ይልቃል ቢተው እንደገለጹት፣ ይህ እጅግ ዘመናዊ የሆነ ፕሮጀክት በዚህ ሳምንት ውስጥ በይፋ ለህዝብ ይቀርባል ብለዋል።
ይህ ቴክኖሎጂ በሀገሪቱ ያለውን የጸጥታና የደህንነት ጥበቃ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት ለመከላከል በሚያስችል መልኩ የተቃኘ መሆኑ ተገልጿል። ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ይፋ ሲያደርግ ዝርዝር የአሰራር ሂደቱንና የቴክኖሎጂውን አቅም ለህዝብና ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያብራራ ይጠበቃል።
