0
#FastMereja I የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ልማት አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የግል ሕይወታቸውን እንኳን መምራት ያልቻሉ ግለሰቦች ስለ “ሽግግር መንግሥት” ምስረታ ማውራታቸው አግባብነት የሌለውና “ወለፈንዲ” መሆኑን ገለጹ።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካው መድረክ ስለ ሽግግር መንግሥት የሚደመጡ ድምጾችን በዝምታ እንደማያልፏቸው አመልክተዋል። አማካሪው በጽሁፋቸው “ሕይወታቸውን እንኳን ያላሸጋገሩ ሰዎች ስለ ሽግግር መንግሥት ሲያወሩ እንደ መስማት ያለ ወለፈንዲ የለም” ብለዋል።
ይህ አስተያየት በተለይ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ግፊት እያደረጉ ባሉበት ወቅት የተሰነዘረ ሲሆን፣ ከመንግሥት ወገን የተሰጠ ጠንከር ያለ ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል።
መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.
