banner

የደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን የመራሔ ብርሃናት ሰንበት ትምህርት ቤት የ22 ሚሊዮን ብር የሕንጻ ማጠናቀቂያ የገቢ ማ

የደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን የመራሔ ብርሃናት ሰንበት ትምህርት ቤት የ22 ሚሊዮን ብር የሕንጻ ማጠናቀቂያ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቀረበ!

#Fastmereja:በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የሚገኘው አንጋፋው የመራሔ ብርሃናት ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የጀመረውን ባለ አምስት ፎቅ ሁለገብ የትምህርት ሕንጻ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የ22 ሚሊዮን ብር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ለ62 ዓመታት በቤተክርስቲያንና በሀገር ግንባታ ላይ ጉልህ ሚና ያላቸውን ምሁራንና አገልጋዮችን ሲያፈራ የቆየው ይህ ሰንበት ትምህርት ቤት፤ በአሁኑ ወቅት ከ2,500 በላይ ሕጻናትና ወጣቶችን በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአገልግሎት ስፋቱና የተማሪዎች ቁጥር መጨመር ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን አስፈላጊ ስላደረገው፣ የሕንጻውን 5ኛ ፎቅ ግንባታ ለማጠናቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

የሰንበት ትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንደገለጸው፣ የግንባታ ቁሳቁስ ዋጋ መናርና የአካባቢው ነዋሪዎች በኮሪደር ልማት ምክንያት መራቃቸው ግንባታው በታቀደው ፍጥነት እንዳይጠናቀቅ እንቅፋት ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ”ለእናት መራሔ ብርሃናት ሰ/ት/ቤት ከምሸት እስከ ንጋት” በሚል መሪ ቃል ልዩ የኦንላይን (Online) የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በዚህ መንፈሳዊ መርሃ ግብር ላይ ታዋቂ ስብክያነ ወንጌል፣ መዘምራንና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቤተክርስቲያኗ ልጆችና የቅዱስ ዑራኤል ወዳጆች በተለያዩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሕጻናትና ለደካሞች ምቾት የሚሰጥ አሳንሰር (Lift) የሚገጠምለት ሲሆን፣ ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችንና የስልጠና ማዕከላትንም ያካትታል።

የቀጥታ ስርጭት መከታተያ ማህበራዊ ገጾች
https://youtu.be/@merahe22
facebook @merahe 22
Tiktok @merahe 22

የባንክ አካውንቶች
cbe: 2221
አባይ ባንክ : 2222
ቴሌ ብር 0949-09-83-01
Cashapp- $merahe22
Zelle – 4044726429
(Alazar Tefera)

https://gofund.me/b8d76506f

ስልኮች
+251 977-25-22-22
+251 910-00-78-95
+251 949-09-83-01





Leave a Comment