0
#FastMereja I በሲ ኤም ሲ መስመር በተባበሩት አደባባይ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት መንገዱ ለትራፊክ ዝውውር ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ የማሳሰቢያ መረጃ፣ በአደባባዩ ላይ በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ሳቢያ የተፈጠረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረት መንገዱ እንዲዘጋ መደረጉን ገልጿል። በዚህም ምክንያት ወደ አደባባዩ የሚያመሩ አሽከርካሪዎች ለተጨማሪ መዘግየትና እንግልት እንዳይዳረጉ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
አደጋው ያስከተለው የጉዳት መጠን በዝርዝር ባይገለጽም፣ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በስፍራው ተገኝተው የትራፊክ ፍሰቱን ለማስተካከልና መንገዱን ክፍት ለማድረግ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ታውቋል። አሽከርካሪዎች አካባቢው ላይ የሚታየው መጨናነቅ እስኪቀልል ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁና ለትራፊክ ባለሙያዎች ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
