0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የሸቀጦች እጥረት እንዳይከሰትና ገበያው እንዲረጋጋ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ቢሮው በተለይ የሥጋ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በአንድ ኪሎ 650 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የነዳጅ እጥረት በምርት ስርጭት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ካለፈው ወር ጀምሮ ከክልሎች ጋር የተቀናጀ የምርት ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። ለዚህም በከተማዋ 6 ዋና ዋና ማዕከላት፣ 246 የሰንበት ገበያዎች እና ከ2 ሺህ በላይ የኅብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በቂ ምርት እንዲያቀርቡ ተዘጋጅተዋል።
በበዓሉ ወቅት የዋጋ ንረትና የንግድ ማጭበርበርን ለመከላከል ቢሮው ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ኃይል ያሰማራ ሲሆን፤ ያለአግባብ ዋጋ በሚጨምሩና በሚዛን በሚያጭበረብሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
