banner

ከገንዘብ በላይ የታማኝነት ልክ

​#FastMereja I በብሔራዊ ሙዚየም የትኬት ሽያጭ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ጌራወርቅ አሰፋ፣ አንድ ቻይናዊ ጎብኝ የዘነጋውን 47 ሺህ ብር የያዘ ቦርሳ በታማኝነት በመመለስ የሀገርን ገጽታ የሚያስከብር ተግባር ፈጽመዋል።

​የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ሶንግ ጆንግ የተባለ ቻይናዊ ጎብኝ ከጓደኞቹ ጋር በብሔራዊ ሙዚየም ያደረገውን ጉብኝት አጠናቆ ሲወጣ፣ 47 ሺህ የኢትዮጵያ ብር የያዘ ቦርሳውን ዘንግቶት ነበር። ቦርሳው የወደቀው በትኬት መቁረጫ መስኮት አካባቢ ሲሆን፣ ወ/ሮ ጌራወርቅ አሰፋ ቦርሳውን እንዳገኘች ለባልደረቦቿ በማሳወቅ በጥንቃቄ ጠብቃ እንዲቆይ አድርጋለች።

​ከአራት ሰዓታት በኋላ ቻይናዊው ጎብኝ በከፍተኛ ጭንቀት ወደ ሙዚየሙ ቢመለስም፣ የጠፋበትን ገንዘብ አንድም ሳንቲም ሳይጎድል ተረክቧል። ወ/ሮ ጌራወርቅ ለኤኤምኤን (AMN) በሰጠችው ቃል፣ “ገንዘቡን ስመልስ ከእሱ በላይ ትልቅ ሸክም እንደወረደልኝ ተሰምቶኝ እፎይታ አግኝቻለሁ” ስትል ገልጻለች።

​ጎብኚው ሶንግ ጆንግ በኢትዮጵያውያን ቅንነት እጅግ መገረሙን በመግለጽ፣ የወ/ሮ ጌራወርቅን ታማኝነት የሚገልጽ የምስጋና ማስታወሻ በገዛ እጁ አስፍሯል።

​የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የብሔራዊ ሙዚየም መሪ ስራ አስፈፃሚ፣ ለባለሙያዋ የምስጋና ደብዳቤና እውቅና መስጠታቸውን አስታውቀዋል። ይህ ተግባር በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ትልቅ የሥነ-ምግባር አርአያ ተደርጎ ተወስዷል።

Leave a Comment