0
#FastMereja I በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ፣ የድሉ ባለቤትና የጨዋታው ኮከብ የሆነው አጥቂው ፍፁም ጥላሁን ድሉን ከሦስት ዓመት በፊት ለሞተችው እናቱ በመስጠት በስሜት ተሞልቶ በእንባ ታጅቦ ምስክርነቱን ሰጥቷል።
ለቅዱስ ጊዮርጊስ የድል ግብ በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ፍፁም ጥላሁን፣ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሜዳው ውስጥ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መላውን ስፖርት አፍቃሪ ያስለቀሰ ንግግር አድርጓል።
አጥቂው የነገው ቀን እናቱ ካረፈች ሦስተኛ ዓመቷ መሆኑን ገልጾ፣ በህይወት እያለች ካሰበው ደረጃ ላይ ሊያደርሳት ባለመቻሉ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። “እናቴን እወዳታለሁ፤ ነፍሴን ለእርሷ መቀየር ብችል እቀይራት ነበር” ያለው ፍፁም፣ እናቱ በህይወት ዘመኗ ብዙ መከራና ችግር እንዳሳለፈች እንዲሁም “እንደ ሰው ሳይደላት” ማለፏ የሁልጊዜ ቁጭቱ መሆኑን በለቅሶ ተናግሯል።
ተጫዋቹ ጨምሮም “ሰው ሳላደርግሽ ስለሞተሽብኝ አዝናለሁ፣ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው” በማለት ለቤተሰቦቹና ለሟች እናቱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ተናግሯል።
