banner

ከ40 ቀናት መዝጊያ በኋላ በአል-አቅሳ መስጂድ የፈጅር ሶላት ተከናወነ

​#FastMereja I በኢየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሳ መስጂድ በእስራኤል ባለስልጣናት ለ40 ቀናት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ፣ ዛሬ ሐሙስ በመጀመሪያው የፈጅር (የለሊት) ሶላት ላይ ወደ 3,000 የሚጠጉ ምዕመናን መሳተፋቸውን የአል-ቁድስ ገዢ መሥሪያ ቤት አስታወቀ።

​ምዕመናኑ ወደ ስፍራው መግባት የቻሉት በእስራኤል የደህንነት ኃይሎች በኩል ከፍተኛ የፍተሻ እና የጥበቃ እርምጃዎች በነበሩበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል። ሆኖም በሂደቱ ላይ አንዳንድ ምዕመናን ጥቃት እንደደረሰባቸው መሥሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።

Leave a Comment