0
#FastMereja I በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእምነት ተከታዮች ዘንድ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትህትና እና የምስጢረ ቁርባን መመስረትን የሚያዘክረው የፀሎተ ሐሙስ በዓል ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ መንፈሳዊ ክንውኖች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሃይማኖት አባቶች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በተገኙበት እየተከናወነ በሚገኘው የዕለቱ መርሃ-ግብር፤ የሕፅበተ እግር (የእግር ማጠብ) ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። ይህ ስርዓት ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያስተማረውን የትህትና እና የፍቅር አርአያነት የሚያስታውስ መሆኑን የሃይማኖት አባቶች በዕለቱ ትምህርታቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።
📷 AMN



