banner

አርቲስት ቴዲ አፍሮ የሀዲያን እሴት “ሴሌሜን” ለአለም በማስተዋወቁ እውቅና ተሰጠው

​#FastMereja I ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የሀዲያ ብሔር ዝነኛ የባህል እሴት የሆነውን “ሴሌሜ” በማቀንቀንና ለአለም በማስተዋወቅ ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበረከተለት።

​ይህ እውቅና የተሰጠው የሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ባዘጋጀው “ሴሌሜ ለሰላም” ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ ነው። “ሴሌሜ” የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቅርቡ “ረጅሙ የጎዳና ላይ ትርዒት” በሚል በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ መመዝገቡ ይታወሳል።

​ቴዲ አፍሮ “ሴሌሜ ሴሌሜ ቦያ ሴሌሜ” በተሰኘው ተወዳጅ የሙዚቃ ስራው የብሔሩን ባህላዊ ዳንስና ዜማ በሰፊው እንዲታወቅ ማድረጉ በምስጋና መርሃ-ግብሩ ላይ ተገልጿል።

Leave a Comment