banner

አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ላይ የፍርድ ቤት ድል ተቀዳጁ

​#FastMereja I በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከአገር ለማስወጣት የጀመረውን ሙከራ በመቃወም የከፈቱትን የሕግ ክርክር በድል አጠናቀዋል። የፌዴራል ፍርድ ቤት የአስተዳደሩን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ኢትዮጵያውያኑ በቆይታቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል።

​በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የአሜሪካ መንግስት፣ “ጊዜያዊ የጥበቃ ፍቃድ” (TPS) ተጠቃሚ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የቆይታ ጊዜያቸው እንዲያበቃና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም የቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል። ዳኛው በሰጡት ብይን፣ አስተዳደሩ ጥበቃውን ለማቋረጥ የተጠቀመበት አካሄድ የሕግ ስህተት ያለበትና በቂ ማስረጃ ያልቀረበበት መሆኑን ገልጸዋል።

​ይህ ውሳኔ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ በነፃነት የመኖርና የመሥራት መብታቸውን የሚያስጠብቅላቸው ሲሆን፣ ከአገር የመባረር ስጋት አንዣብቦባቸው ለነበሩ ቤተሰቦች ትልቅ እፎይታ ሆኗል። የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ውሳኔው የአስተዳደሩን የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች የሚገታና ለቀጣይ መሰል ጉዳዮች እንደ አርአያ የሚጠቀስ ነው።

​መንግስት በበኩሉ በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ባይገልጽም፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ መሪዎች ግን ውጤቱን “የፍትህ ድል” ሲሉ አወድሰውታል።

Leave a Comment