0
#FastMereja I የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) እስራኤል በተለያዩ የሊባኖስ አካባቢዎች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በጽኑ እንደምታወግዝ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ድርጊቱ በቀጠናው ደህንነትና መረጋጋት ላይ የሚያስከትለው መዘዝ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረበት ገልጿል። ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ አለም አቀፍ ጥረቶች እንዲጠናከሩ የጠየቀው መግለጫው፣ በዓለም አቀፍ ህግጋት መሰረት ለንጹሃን ዜጎች ሙሉ ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል።
ኤምሬትስ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሊባኖስ መንግስት ጋር ያላትን ሙሉ አብሮነት የገለጸች ሲሆን፣ የሀገሪቱን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት ታማኝነት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለች። ማንኛውም አለመግባባት በግጭት ሳይሆን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታት እንዳለበትም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
