0
#FastMereja I የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው ሊባኖስን ብቻዋን እንደማትተዋት በመግለጽ፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን “በግልጽ መጣስ” ነው ሲሉ ኮነኑ።
ፕሬዝዳንቱ እስራኤል ጥቃቷን የምትቀጥል ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች ትርጉም አልባ እንደሚሆኑ አስጠንቅቀዋል። “እጃችን በቃታ ላይ ነው፤ ኢራንም የሊባኖስን ህዝብ አሳልፋ አትሰጥም” ሲሉ ፔዜሽኪያን ያላቸውን ጽኑ አቋም ገልጸዋል።
ይህ የኢራን ማስጠንቀቂያ የተሰማው ውጥረቱን ለማርገብ ጥረቶች እየተደረጉ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ ድርጊቱ ቀጠናውን ወደ በለጠ ግጭት ሊከተው እንደሚችል ተሰግቷል። እስካሁን ከእስራኤል ወገን ለተሰነዘረው ወቀሳ የተሰጠ ምላሽ የለም።
