0
#FastMereja I የኢራን የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂካዊ ምክር ቤት ኃላፊ ካማል ካራዚ፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል የአየር ጥቃት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ይፋዊ የዜና ወኪል ኢርና ዘገበ።
በኢራን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የነበራቸው እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ካማል ካራዚ፣ ህይወታቸው ያለፈው በጦርነቱ ወቅት በተሰነዘረ የአየር ጥቃት በደረሰባቸው ጉዳት መሆኑ ተረጋግጧል። ኃላፊው በኢራን ከፍተኛ አመራሮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የነበራቸው ሲሆን፣ ህይወታቸው ማለፉ በወቅታዊው የቀጣናው ውጥረት ላይ ተጨማሪ ትኩረት እንዲያርፍ አድርጓል።
