banner

ድምፃዊ ወንድሙ ጅራ በመድኃኒዓለም ትምህርት ቤት የክብር አምባሳደር ተደርጎ ተሾመ

​#FastMereja I ታዋቂው ድምፃዊ ወንድሙ ጅራ “የኔ ትዝታ” በተሰኘው የሙዚቃ ስራው የትምህርት ቤቱን ታሪክ በማስተዋወቅና ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ በመድኃኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክብር አምባሳደርነት ሹመት ተሰጠው።

​በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የመድኃኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ ድምፃዊ ወንድሙ ጅራ ለትምህርት ቤቱ ላበረከተው አዎንታዊ ተጽዕኖ የእውቅና እና የክብር አምባሳደርነት የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።

​ድምፃዊው “የኔ ትዝታ” በተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮው ላይ የትምህርት ቤቱን እውነተኛ ታሪክ እና የቀድሞ ትውስታዎችን በማካተቱ፣ ለተቋሙ ታላቅ የፕሮሞሽን ስራ እንደሰራ ተገልጿል።

​መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

Leave a Comment