#FastMereja I በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአርሲ ሀገረ ስብከት፣ በሮቤ ወረዳ ቤተክህነት ስር የሚገኘው ታሪካዊው የጨፌ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፤ እያከናወነ ያለውን አዲስ የህንጻ ግንባታ ለማጠናቀቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ይህ ታላቅ መንፈሳዊ ባዛር ከሚያዝያ 16 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሮቤ ከተማ በድምቀት ይካሄዳል። የህንጻ ግንባታው አሁን ባለበት ደረጃ ላይ ደርሶ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የሁሉንም ምዕመናን፣ የደብሩ ወዳጆች እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (Diaspora) ድጋፍ እንደሚሻ የባዛር አዘጋጅ ኮሚቴው ገልጿል።
በቦታው በመገኘት ድጋፍ ማድረግ ለማይችሉ ምዕመናን የሚከተሉት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ቀርበዋል፦
✒️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000165685222
✒️ አቢሲኒያ ባንክ፦ 133063455
✒️ ኦሮሚያ ባንክ፦ 1074880231211
✒️ አዋሽ ባንክ፦ 013521287505900
የሂሳብ ስም፦ ጨፌ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ህንጻ ስራ
በዕለቱ ተገኝታችሁ፣ ቤተሰቦቻችሁንና ጓደኞቻችሁን በማስተባበር የቅዱስ ገብርኤልን ቤት በማነጽ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
