banner

አርሰናል በደጋፊው ተከሰሰ፡ “የቡድኑ ደካማ አፈጻጸም ለከፍተኛ የስነ-ልቦና ቀውስ ዳርጎኛል”

​#FastMereja I ኤሪክ ኪያማ የተባለ ዩጋንዳዊ የአርሰናል ደጋፊ፣ ክለቡ ለከፍተኛ ስሜት መቃወስ፣ ጭንቀት እና ስነ-ልቦናዊ ጫና ዳርጎኛል በሚል ክስ መሰረተ። ደጋፊው አርሰናል በበርንማውዝ ከተሸነፈ በኋላ ባስገባው የክስ ደብዳቤ፣ የክለቡ አሁናዊ አቋም “ተቀባይነት የሌለው” መሆኑን ገልጿል።

​በዩጋንዳ የሚኖረው ግለሰብ በክሱ ላይ እንደጠቀሰው፣ ተጫዋቾቹ እና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሙያዊ ግዴታቸውን በብቃት መወጣት ተስኗቸዋል። ደጋፊዎች ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለክለቡ እንደሚሰጡ የጠቀሰው ኪያማ፣ ቡድኑ የሚያሳየው ደካማ ጥረት “ሊጠየቅበት የሚገባ የስነ-ልቦና ስቃይ” እያደረሰብኝ ነው ሲል ተከራክሯል።

​ክስ አቅራቢው ጉዳዩ ወደ ከፍተኛ የህግ ክርክር ከማምራቱ በፊት ክለቡ ሁለት ነገሮችን እንዲያደርግ በደብዳቤው ጠይቋል፦ ​ከክለቡ በኩል ይፋዊ ማብራሪያ እንዲሰጠው፣ ​የቡድኑን ተወዳዳሪነት በአፋጣኝ ለመመለስ የሚያስችል ግልጽ እቅድ እንዲቀርብ።

​እነዚህ ጥያቄዎች የማይመለሱ ከሆነ፣ በስፖርታዊ ውጤቱ ላይ ባደረገበት “የእምነት ክህደት” እና በደረሰበት ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የካሳ ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። ክለቡ አርሰናል እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ምላሽ የለም።

​ሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም.

Leave a Comment