0 #FastMereja I ጋሞ ጨንቻ የኢትዮጵያን ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ ውድድርን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን በዛሬው ዕለት አረጋግጧል። ዛሬ በተደረገው ወሳኝ ጨዋታ ጋሞ ጨንቻ የቡራዩ ክፍለ ከተማን ቡድን 3-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። ይህን ተከትሎም ክለቡ በአጠቃላይ 41 ነጥቦችን በመሰብሰብ በምድቡ የነበረውን የበላይነት አስጠብቆ ወደ ላቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ እርከን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀላቅሏል።