banner

የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

​#FastMereja I የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አማካሪ የነበሩት ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም በ46 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ዛሬ ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ቦታቸው በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።

​ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ለ11 ዓመታት (ከ2003 እስከ 2014 ዓ.ም) ወረዳቸውን በመወከልና በተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ አባል በመሆን አገልግለዋል። ከመስከረም 2014 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማካሪነት ሲሰሩ ቆይተዋል።

​ከባለቤታቸው ከዶ/ር ሀብቴ ጅፋር ጋር ትዳር መስርተው የአንድ ወንድና የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበሩ።

​የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

​ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

Leave a Comment