banner

ባልተገኙ አትሌቶች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ሊወሰድ ነው

​#FastMereja I የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን የውድድር መርሃ-ግብር ላይ ተመዝግበው ሳይገኙ በቀሩ አትሌቶች ላይ ጥብቅ የዲስፕሊን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ። ፌዴሬሽኑ አትሌቶቹ በከሰዓቱ ውድድር ላይ እንዲገኙ የመጨረሻ ጥሪ አስተላልፏል።

​በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቀድመው ምዝገባ ቢያካሂዱም፣ በጠዋቱ መርሃ-ግብር ላይ ያልተገኙ መኖራቸው ተገልጿል። ይህ መቅረት በውድድሩ ሂደት ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን የጠቆመው ፌዴሬሽኑ፣ ድርጊቱ የስፖርታዊ ጨዋነት መመሪያን የሚጥስ መሆኑን አሳስቧል።

Leave a Comment