banner

ለጄቱር ተሽከርካሪዎች የተገነባው ዘመናዊ የድህረ-ሽያጭ ማዕከል ተመረቀ

​#FastMereja I ሱዌይስ ሞተርስ በኢትዮጵያ ለሚያስገባቸው የጄቱር (Jetour) ብራንድ ተሽከርካሪዎች የጥገና እና የኦሪጅናል Spare Part አቅርቦት አገልግሎት የሚሰጥ አዲስ ማዕከል ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ አስመረቀ።

የኩባንያው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተገለጸው፤ ማዕከሉ በሃገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የጄቱር ተሽከርካሪዎች ቁጥር ተከትሎ የሚነሳውን የደንበኞች የአገልግሎት ፍላጎት በዘላቂነት ለመመለስ ታስቦ የተገነባ ነው።

​ይህ አዲስ የድህረ-ሽያጭ ማዕከል በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች የተደራጀ ሲሆን፣ በተለይም በሃገሪቱ በስፋት እየገቡ ያሉ አዳዲስ የሃይል አማራጭ ያላቸውን የኤሌክትሪክ (EV) እና የሃይብሪድ ተሽከርካሪዎችን በብቃት ለመጠገን የሚያስችሉ ልዩ ወርክሾፖችንና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን መያዙ ተነግሯል።

​ሱዌይስ ሞተርስ ወደዚህ ዘመናዊ መዋቅራዊ ኢንቨስትመንት መግባቱ በኢትዮጵያ በፈጣን ዕድገት ላይ የሚገኘውን የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ሥነ-ምህዳር ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ለማሸጋገር እና አስተማማኝ የረጅም ጊዜ የገበያ መገኘትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።





Leave a Comment