0
#FastMereja የሐበሻ ቢራ አምራች ኩባንያ (Habesha Breweries) በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አስተናጋጅነት በተካሄደው “ብራንድ አፍሪካ 100” (Brand Africa 100) የሽልማት መድረክ ላይ “የኢትዮጵያ ተወዳጅ የቢራ ምርት ስም” (Ethiopia’s Most Admired Beer Brand) በመሆን መመረጡን አስታወቀ።
ኩባንያው ይህንን ሽልማት ያገኘው የሀገሪቱን ባህል፣ ቅርስ እና ማንነት በምርቱ ውስጥ ጠብቆ በማቆየትና የኢትዮጵያን ባህል ለሚያስተዋውቁ ወገኖች እውቅና በመስጠት ለሚያበረክተው አስተዋፅኦ እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ሽልማት ኩባንያው ጥራትንና የአገሬው በቀል ጥበብን አጣምሮ ለመጓዝ የገባውን ቃል የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጹት የሐበሻ ቢራ ኃላፊዎች፣ እያንዳንዱ ጠርሙስ ምርት የኢትዮጵያውያንን ኩራትና ትክክለኛ ማንነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኩባንያው በዚሁ የፓን አፍሪካ መድረክ ላይ ባገኘው እውቅና ኩራት እንደተሰማውና እሴቶቹን ጠብቆ ምርቱን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰራም አክሏል። ለዚህ ስኬት ላበቁት ደንበኞቹና አጋሮቹም “የሚያረካ…ይሸለማል” በሚለው መርህ ምስጋናውን አቅርቧል።


