banner

የአለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋና ባለቤቷ ያሳነጹት የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተመረቀ

​#FastMereja I በአለም ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትግስት አሰፋ እና በባለቤቷ አሰልጣኝ እዮብ ኤልያስ ከፍተኛ የገንዘብና የጉልበት አስተዋፅኦ የተገነባው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ትናንት በድምቀት ተመርቋል። ህንጻ ቤተክርስቲያኑ የተገነባው በሸገር ሀገረ ስብከት፣ በሱሉልታና መነአቢቹ ክፍለ ከተማ ቤተክነት ክልል ውስጥ ልዩ ስሙ “ሚዛን አትሌት መንደር” በሚባለው ስፍራ ላይ ነው።

​የቤተክርስቲያኑን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት መርቀው የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ናቸው። ብፁዕነታቸው ለቤተክርስቲያኑ ግንባታ መሳካት መላውን ንብረታቸውንና ጉልበታቸውን ላፈሰሱት አትሌት ትግስት አሰፋ እና አሰልጣኝ እዮብ ኤልያስ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

​በዕለቱም ለጥንዶቹ ባበረከቱት ከፍተኛ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አማካኝነት የክብር ካባ የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል። ይህ መንፈሳዊ ተቋም በአካባቢው ለሚገኙ ምዕመናን ትልቅ የአገልግሎት ማዕከል እንደሚሆን በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

Leave a Comment