0
#FastMereja I የሕጻናት መጻሕፍት ደራሲዋ ታቲያና ክፍሌ ዛሬ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍትን አስመርቃለች። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው “ፊሽታ” የተሰኘው መጽሐፍ አራተኛው ክፍል ሲሆን፣ ሁለተኛው መጽሐፍ “የንግሥተ ሳባ” የታሪክ መጽሐፍ ሲሆን፣ ከተለያዩ መጻሕፍት በማንበብ፣ ከሁሉም ታሪኮች በማቀናጀት ለህጻናት በሚመች መልኩ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ደራሲ ታቲያና ባደረገችው ንግግር “ልጆቻችንን ዓለም ከሚያሳድገው በየቤተ እምነቶቻችን አሳድገን መልካም ትውልድ፣ ነገም አገር የሚረከብ ትውልድ እንድናፈራ” ብላለች።
መጻሕፍቱ በየቤተ መጻሕፍቱ ለማሰራጨት እየተሞከረ ሲሆን፣ ለጊዜው በአምስት መጻሕፍት መደብር እና በአማዞን ድረ-ገጽም የሚገኙ ይሆናል። መጻሕፍቱ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅተዋል።
ደራሲ ታቲያና፣ ፊሽታ የተሰኘው መጽሐፍ ከሶስት አመት በላይ ጥረት የተደረገበት እና ለተለያዩ የእድሜ ክልሎች ተደራሽ እንዲሆን የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች።




