banner

በሳዑዲ አረቢያ 34 ኪሎ ግራም ሀሺሽ ወደ ሀገሪቷ ሊያስገቡ ሲሉ 4 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

​#FastMereja | የሳዑዲ አረቢያ የድንበር ጠባቂ ኃይል በአሲር ክልል 34 ኪሎ ግራም የሐሺሽ አደንዛዥ ዕፅ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሲሞክሩ የነበሩ አራት ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

​የሀገሪቱ የድንበር ጠባቂ የመሬት ላይ ጥበቃ አባላት በአሲር ክልል ስር በሚገኘው የራቡአ ቀጠና ተጠርጣሪዎቹ የድንበር ደህንነት ህግን ጥሰው አደንዛዥ ዕፁን ለማስገባት ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።

የሳዑዲ አረቢያ የሚመለከታቸው አካላት እንደገለጹት፣ በተጠርጣሪዎቹ ከተያዘው ዕፅ ጋር ወደሚመለከተው የፍትህ አካል እንዲተላለፉ ተደርጓል።

Leave a Comment