0
#FastMereja I በቅርቡ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ ያለፈው የቅዱሳን ይርጋለም እህት ሩት ይርጋለም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው ፈጣንና የተቀናጀ ክትትል የተሰማትን ከፍተኛ ምስጋና ገለጸች።
ሩት በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈችው መልዕክት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው የጠበቀ ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ሳይበተኑ እና ልብሳቸውንም ሳይቀይሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጻለች። ይህ ክስተት የአንድ ቤተሰብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ህብረተሰብ ጉዳይ መሆኑን ያመለከተችው ሩት፣ መሰል አስቃቂ ድርጊቶች በሌሎች ቤተሰቦች ላይ እንዳይደገሙ ሲባል ለቅዱሳን ትክክለኛና ተመጣጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቃለች።
ህዝቡም ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረትና ያሳየውን አጋርነት በማመስገን፣ ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ህዝቡ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪዋን አስተላልፋለች።
