banner

በደብረ ብርሃን የቡሄ በዓል ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቹን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ

#FastMereja I በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶቹን በጠበቀ መልኩ በተለያዩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች በከፍተኛ ድምቀት መከበሩ ተገለጸ።

ባለሐገሩ አስጎብኚ ድርጅት ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ በዓል ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት በታላቅ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በስነ-ስርዓቱ ወቅት የቡሄ በዓል መገለጫ የሆኑት የጅራፍ ማጮህ፣ የሙልሙል ዳቦ መጋገር እና ስጦታ፣ የችቦ መለኮስ እንዲሁም የቡሄ ጨዋታዎችና ባህላዊ ዜማዎች በስፋት ቀርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለፀው በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከማከበር ባለፈ ለቀጣይ የቱሪዝም እንቅስቃሴና ለባህል እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ሁነቱ የአካባቢውን መልካም ገጽታ ከማሳወቅ ባሻገር የማህበረሰቡን አንድነትና ወንድማማችነት የበለጠ ያጠናከረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሥራ መሪዎች፣ የባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።





Leave a Comment