banner

ከድንጋይ ወፍጮ እስከ ዓለም አቀፍ የቅመማ ቅመም ኤክስፖርት ፋብሪካ

​#FastMereja I በድንጋይ ወፍጮ እርድ እየፈጨች ባሳደገቻቸው እናቷ ልፋት የተነሳሳችው ወይዘሮ ሔዋን ቀለመወርቅ ዘመናዊ እና ደረጃውን የጠበቀ የ’HEWAN SPICE’ ቅመማ ቅመም ፋብሪካን በደብረብርሃን አቋቁማ እየሰራች ይገኛል።

በ730 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ፋብሪካው ከ30 በላይ የተፈጥሮ የኢትዮጵያ ቅመሞችን በማዘጋጀት ከሀገር ውስጥ አልፎ በዱባይ፣ ቶሮንቶ፣ ለንደን፣ ኒውዮርክ እና በአማዞን (Amazon) አማካኝነት ለዓለም ገበያ ማቅረብ ጀምሯል።

​በልጅነቷ የእናቷን እንግልት ስታይ “የእናቴን ልፋት ወደ ማሽን እቀይራለሁ” በማለት የገባችውን ቃል እውን አድርጋ በአሁኑ ወቅት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር እየሰራች ትገኛለች።

​ፋብሪካው ዋና አላማው አዳዲስ የስራ እድሎችን መፍጠር፣ ሴቶችን ማብቃት እና “Made in Ethiopia” የሚለውን ምርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስጠራት እንደሆነ ተገልጿል። መስራቿ ለሴቶች ባስተላለፈችው መልዕክት ህልማቸው ትልቅ በመሆኑ ምክንያት ማንንም እንዳይፈሩ እና በትዕግስት፣ በእምነት እንዲሁም በድፍረት ወደፊት እንዲገፉ ጥሪ አቅርባለች።





Leave a Comment