0 #FastMereja I የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚካሄደው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ በብቸኝነት በዕጩነት መቅረባቸውን ይፋ አደረገ። ኮሚቴው የጠቅላላ ጉባኤ አባላት እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያቀረቧቸውን ዕጩዎች ሰነድ መርምሮና አጣርቶ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በፕሬዝዳንትነት ደረጃ የቀረቡት ብቸኛው ተወዳዳሪ አምባሳደር አቶ ኢሳያስ ጅራ መሆናቸው ተረጋግጧል።