0
#FastMereja I በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ በሚገኘው አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፣ ዓመታዊው የ”ዓይኒ ዋሪ” በዓል “ዓይኒ ዋሪ ለዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ወዳጅነት” በሚል መሪ ቃል በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የከተማዋ ልጃገረዶች ባህላዊ አልባሳቶቻቸውን በመልበስና ያጌጡ ጌጣጌጦችን በማድረግ «እመቤቴ ሆይ፣ መጣሁልሽ ቃሌን ልፈጽም» የሚሉ ባህላዊና መንፈሳዊ የደስታ ዜማዎችን በመዘመር ምስጋናቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ። በበዓሉ ላይ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች እና እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ የከተማዋን ባህላዊና ታሪካዊ ገጽታ በደመቀ ሁኔታ የሚያንጸባርቁ ስነ-ስርዓቶች በመከናወን ላይ ናቸው።
