በመርካቶ ከ900 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ያካተተው “የበጎነት መንደር” ተመርቆ ለነዋሪዎች ተላለፈ
#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ በመርካቶ አካባቢ “ቅጠል ተራ” የተገነባውና 960 መኖሪያ ቤቶችን የያዘው “የመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር” ግንባታው ተጠናቆ ለተፈናቃይ ነዋሪዎች መተላለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
ፕሮጀክቱ በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በአራት ወራት የሌሊትና የቀን የፈጠነ ግንባታ ሂደት የተጠናቀቀ ነው። መንደሩ ባለ ዘጠኝ ወለል (G+9) የሆኑ ዘጠኝ ህንፃዎችን የሚያካትት ሲሆን፤ ከ960 መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ 371 የንግድ ሱቆችን፣ የህፃናት መጫወቻዎችን፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶችን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በውስጡ አሟልቷል።
በተጨማሪም ለኤሌክትሪክ መኪናዎች ቻርጅ ማድረጊያ፣ ዘመናዊ የሊፍት፣ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች እንዲሁም የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ እንደተዘጋጀለት ተገልጿል። ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መረጃ፥ አካባቢው ቀደም ሲል ለኑሮ አስቸጋሪ፣ የተጨናነቀ እና በተደጋጋሚ በእሳት አደጋ የሰው ህይወትና ንብረት የሚጠፋበት እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን ለዜጎች ክብር በሚመጥን መልኩ ሙሉ በሙሉ መለወጡን ገልፀዋል።







\u1260\u1218\u122d\u12ab\u1276 \u12a8900 \u1260\u120b\u12ed \u1218\u1296\u122a\u12eb \u1264\u1276\u127d\u1295 \u12eb\u12ab\u1270\u1270\u12cd \