banner

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲን የሚያገናኝ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ሊዘረጋ ነው

​#FastMereja – በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነ አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።

​ይህ በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያው ደወሌ የሚያገናኘው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ይፋ የተደረገው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና በታዋቂው ናይጄሪያዊ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ተሳትፎ ነው።

​ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ማለትም በዳመርጆግ እና በደወሌ በሚገነቡ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ ሲሆን፤ ግንባታውም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረገ ጥምረትና አጋርነት የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።

​ይህ ታሪካዊ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ለነዳጅ ትራንስፖርት የሚወጣውን የሎጂስቲክስ ወጪና መዘግየት በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ፣ የኢነርጂ ዋስትናን የማጠናከር እንዲሁም የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የንግድ መስመርን ፍጥነት እና ዘላቂነት የማሳደግ ሚና ይኖረዋል።

​ይህ መሰረተ ልማት ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመርነቱ ባሻገር፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንት እና በጋራ መልማትን ማዕከል ያደረገ፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና አስተማማኝ ለሆነ የጋራ ኢኮኖሚያዊ እጣ ፈንታ የሚደረግ ሰፊ ኢንቨስትመንት መሆኑ ተነግሯል።

Leave a Comment