banner

\u120b\u1295\u12f5\u121b\u122d\u12ad \u12a0\u1320\u1243\u120b\u12ed \u1206\u1235

ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀንን አከበረ!

#Fastmereja I ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል 8ኛውን የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀን“ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና” እና “ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና ለሙሉ ሕይወት!” በሚል መሪ ቃል በዛሬዉ እለት በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ።

በመክፈቻው መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ እንደገለጹት፤ሆስፒታሉ ቀኑን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሲቀላቀል ለስድስተኛ ጊዜው መሆኑን ገልፀዉ በማይተላለፉ በሽታዎች የሚኖሩ ሕመምተኞች የረጅም ጊዜና የተቀናጀ ሕክምና የሚሹ በመሆናቸው፣ የሕመምተኞች ደህንነት በእያንዳንዱ የሕክምና ሂደት ውስጥ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ፕሮፌሰር ኦሊ አክለውም እያንዳንዱ የሆስፒታሉ ሰራተኛ የታካሚ ደህንነት ባለቤት እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሆስፒታሉ አስተማማኝ አሰራርን ለመገንባት፣ የቡድን ስራን ለማጠናከር እና ታካሚዎችን ማዕከል ያደረገ ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በዕለቱ የታካሚዎችንና የታካሚ ቤተሰቦችን ወክለው ንግግር ያደረጉት ኢንጂነር ፈቲያ መሐመድ በበኩላቸው፤ ለታካሚዎች ደህንነት መከበር የመመሪያዎችና የክትትል ስርዓቶች አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ዋናው መሰረት ግን ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው መሆናቸውን አስምረውበታል።

በተጨማሪ “ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው በቀን 24 ሰዓት ከሕመምተኛው አልጋ አጠገብ ይገኛሉ” ያሉት ኢንጂነር ፈቲያ፤ “በሥራ ብዛት ተወጣጥረው የሚያድሩ የሕክምና ባለሙያዎች ሊያመልጧቸው የሚችሉትን ትንንሽ ነገር ግን ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ቀድመው የማስተዋል እድል እንዳላቸዉ የተገለፀ ሲሆን የታካሚዎችንና የቤተሰቦቻቸውን ድምፅ መስማትና ማክበር ለደህንነታቸው መረጋገጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል” ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱ ሞቶች መካከል 74% የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች (እንደ የልብ ሕመም፣ ካንሰር፣ ስኳርና የረጅም ጊዜ የሳንባ ሕመሞች) ምክንያት የሚከሰቱ ሲሆኑ በተጨማሪም ከ10 ሕመምተኞች መካከል 1 ሕመምተኛ በሕክምና ወቅት ጉዳት የሚደርስበት ሲሆን፣ ከዚህ ጉዳት ውስጥ አጋማሹ (50%) መከላከል የሚቻል ስለመሆኑም ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የታካሚ ቤተሰቦች እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ የሕክምና አሰጣጥ ጥራትንና የታካሚዎችን ደህንነት የበለጠ ለማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።






\u120b\u1295\u12f5\u121b\u122d\u12ad \u12a0\u1320\u1243\u120b\u12ed \u1206\u1235\u1352\u1273\u120d \u12e8\u12d3\u1208\u121d \u12a0\u1240\u134d \u12e8\u1273\u12ab\u121a\u12ce\u127d \u12f0\u1205\u1295\u1290\u1275 \u1240\u1295\u1295 \u12a0\u12a8\u1260\u1228!\n\n#Fastmereja I \u120b\u1295\u12f5\u121b\u122d\u12ad \u12a0\u1320\u1243\u120b\u12ed \u1206\u1235\u1352\u1273\u120d 8\u129b\u12cd\u1295 \u12e8\u12d3\u1208\u121d \u12a0\u1240\u134d \u12e8\u1273\u12ab\u121a\u12ce\u127d \u12f0\u1205\u1295\u1290\u1275 \u1240\u1295\u201c\u1270\u120b\u120b\u134a \u1263\u120d\u1206\u1291 \u1260\u123d\u1273\u12ce\u127d \u12f0\u1205\u1295\u1290\u1271 \u12e8\u1270\u1320\u1260\u1240 \u1215\u12ad\u121d\u1293\

Leave a Comment