banner

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሙሉ ለሙሉ የሥራ ዕድል ያመቻቸላቸውን ተማሪዎች አስመረቀ!

#Fastmereja:-በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በዓለም አቀፉ የቤልጂየም ኩባንያ «ፑራቶስ» (Puratos) ትብብር የተቋቋመው «የፑራቶስ ኢትዮጵያ ዳቦ እና ኬክ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት»ላለፉት 2 አመታት ያሰለጠናቸዉን የመጀመሪያ ዙር 24 ሰልጣኞቹን በዛሬዉ እለት አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ እንደገለጹት፤ መርሃ-ግብሩ ከምረቃ እና ከሰርተፊኬት መስጠት ባለፈ እውቀትን፣ የተግባር ክህሎትን፣ ትጋትን እንዲሁም የትምህርትና የኢንዱስትሪ አጋርነትን ያጎላ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ገልፀዋል።

ተመራቂዎቹ በዳቦ፣ ኬክ እና ቸኮሌት አሰራር ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና የወሰዱት 24ቱም ተመራቂዎች፣ የብሔራዊ የሙያ ብቃት ምዘናን (COC) 100% ማለፋቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በትምህርቱ ጥራትና በሰልጣኞቹ የላቀ ብቃት ምክንያት፣ ሁሉም ተመራቂዎች ገና ሳይመረቁና ከተመረቁ በኋላ ወዲያውኑ እንደ «ካርፉር» (Carrefour) ባሉ ዓለም አቀፍ የችርቻሮ ኩባንያዎች፣ በትልልቅ ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች ውስጥ የሥራ ዕድል ማግኘታቸው ተመልክቷል።

በዳቦና ኬክ አሰራር ዓለም አቀፍ ልምድ ያለው «ፑራቶስ ግሩፕ» ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና አሰራርን ይዞ የመጣ ሲሆን፣ ይኸው አጋርነት ሀገር በቀል አቅምን በማሳደግ ረገድ አርአያነቱ የጎላ መሆኑ ተጠቅሷል።

የፑራቶስ ቤከሪ ስኩል ፋውንዴሽን (Puratos Bakery School Foundation) በተለይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን በሙያ ትምህርት እና በተግባራዊ ስልጠና ማበቃት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።

በምረቃው ወቅት ለተመራቂዎች በተሰጠው የሥራ መመሪያ፤ ምረቃ የትምህርት ማብቂያ ሳይሆን የሙያ ጉዞ መጀመሪያ በመሆኑ ክህሎታቸውን ሁልጊዜ እንዲያሻሽሉ፣ የሥራ ሥነ-ምግባር እንዲያከብሩ እና ከሥራ ተቀጣሪነት ባሻገር ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ ተመክረዋል።

በተጨማሪም ሌሎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሥልጠናቸውን ከእውነተኛው የሥራ ዓለም ፍላጎት ጋር እንዲያጣጥሙ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ አሰሪ ተቋማትም ለነዚህና መሰል ሰልጣኞች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላላፊዎች አሳስበዋል።

Leave a Comment