banner

ቡርኪና ፋሶ ለሰማዕታትና በጦርነት ለጉዳት ለተዳረጉ ዜጎች ነፃ የሕክምና እና የትራንስፖርት አገልግሎት ፈቀደች

#FastMereja I የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ሀገራቸውን ሲከላከሉ ሕይወታቸውን ላጡ ሰማዕታት ቤተሰቦች እና በጦርነት ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ነፃ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ የሕክምና አገልግሎት እና ነፃ ትምህርት የሚያካትት የድጋፍ ፓኬጅ ማጽደቁን አስታወቀች።

​በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ሰብሳቢነት በሳምንቱ መገባደጃ በተካሄደው የካቢኔ ስብሰባ 315 ሰዎች የሀገር “ሰማዕታት” ተብለው የተሰየሙ ሲሆን፣ 10 አካል ጉዳተኞች ደግሞ የሀገር “የጦር ጉዳተኞች” በሚል እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በዚህም መሠረት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችና የሰማዕታት ቤተሰቦች በነፃ የሕዝብ ትራንስፖርትና በሕዝብ ሕክምና ተቋማት ነፃ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቻቸው ደግሞ ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመደብላቸው ተገልጿል።

​የመንግሥት ቃል አቀባይ ፒንግድዌንዴ ጊልበርት ኦዌድራኦጎ እንደተናገሩት፣ ውሳኔው በሀገሪቱ በቅርቡ በተከሰቱት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የደህንነት ቀውስ ወቅት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ዜጎችን ውለታ ለመመለስ እና ለተጎጂ ቤተሰቦች ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

Leave a Comment