banner

“እኛ አሸናፊ ትውልዶች ነን” አቶ ሽመልስ አብዲሳ

#FastMereja I የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በጨፌ ኦሮሚያ ባደረጉት ንግግር፣ ታላቅ አደራና ኃላፊነት የጣለባቸውን ሕዝብ አመስግነው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚፈለገው ደረጃ ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የኦሮሞ ሕዝብ ማንነቱን፣ ነፃነቱን፣ ባህሉንና እሴቶቹን ለማስጠበቅ ውድ መስዋዕትነት ሲከፍል መቆየቱን አስታውሰዋል። የተገኘውን ድል መጠበቅ ብቻውን በቂ አለመሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ፣ ስኬቱን ለማጠናከርና በሁሉም ዘርፍ የበለፀገች ኦሮሚያን ለመገንባት የሁላችንም ድርብ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

“ከባድ ጊዜያትን አሳልፈናል፤ መስዋዕትነትም ከፍለናል፤ በፊታችን ያለው ፈተናና ታግለን የምናልፈው መንገድም ውስብስብ ነው፤ ሆኖም ለማሸነፍ በቁርጠኝነት መስራት አለብን” ሲሉ ገልጸዋል።

እኛ አሸናፊ ትውልዶች በመሆናችን የኦሮሞ ሕዝብ መጻኢ ዕድሉን ለመወሰን እውቀቱን፣ ሙያውንና ክህሎቱን አጠናክሮ መጠቀም እንዳለበት አስገንዝበዋል። የወደፊት ተልዕኳችን ታላቅ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በትዕግስትና በቁርጠኝነት የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በየዓመቱ አዳዲስ ድሎችን ለማስመዝገብ መረባረብ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።









Leave a Comment