0
#FastMereja I በኤርትራ ማዕከላዊ ዞን በገላ-ነፍሒ ንኡስ ዞን ስር በሚገኘው ዓዲ ሓዎሻ አስተዳደር አካባቢ በ11 ሚሊዮን ናቅፋ ገደማ ወጪ የተገነባ አዲስ የውሃ ግድብ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ተመረቀ። ግድቡን የመረቁት በሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ውስጥ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ማጀር ጄኔራል ረመዳን ኦስማን አወልያይ መሆናቸው ታውቋል።
ይህ በአካባቢው ነዋሪዎች እና በሕዝባዊ ግንባታ አስተዋጽኦ በጋራ የተገነባው ግድብ፣ እስከ 180 ሺህ ሜትር ኩብ ውሃ የማከማቸት አቅም ያለው ሲሆን፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብና ለመስኖ ልማት ስራዎችን ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል። በግንባታው ሂደትም የሀገር መከላከያ ኃይል አባላትና ነዋሪዎች ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ወቅት የተገኙ የመንግሥት ባለስልጣናት አካባቢው ያገኘውን ይህን የውሃ ሀብት ህብረተሰቡ በአግባቡና በዘላቂነት እንዲጠቀምበት ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ለግድቡ ግንባታ መሳካት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትና ነዋሪዎች የእውቅና ሰርተፊኬት መሰጠቱን ሻባይት ዘግቧል።







