banner

ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ለሚገኙ አራሶችና ህፃናት ድጋፍ አደረገ!

#Fastmereja:- ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን (Le Enat Charity Foundation) በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ለሚገኙ አራሶችና ህፃናት የተለያዩ የቁሳቁስና የምግብ ድጋፎችን አደረገ።

የህክምና ባለሙያና ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት የእናትፋንታ እንደገለጹት፤ የበጎ አድራጎት ቡድኑ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባደረገው ጉብኝት ለበርካታ አራሶች የንፅህና መጠበቂያዎችን (ሞዴስ) እና ለህፃናት ደግሞ ዳይፐሮችን ያበረከተ ሲሆን በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ለህፃናትና ለአናቶች የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት አብሮነቱን አሳይቷል።

የፋውንዴሽኑ ቦርድና የበጎ አድራጎት ቡድን አባላትን ያሳተፈው ይህ ፕሮግራም፣ ድጋፍ የሚሹ አራሶችንና ህፃናትን ለማገዝ የተደረገ በጎ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን በማቅረብ፣ የጤና ትምህርት በመስጠትና ከኢንፌክሽን ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ረገድ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተመላክቷል።

ለወደፊቱም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙና የንፅህና መጠበቂያዎችን ለመግዛት አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በዘላቂነት ለመደገፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን እዚሁ አገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ እንደሚገኝ መስራቿ ገልጸዋል።

በአሜሪካ የተመሰረተውና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን፤ እስካሁን በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ሞዴስ፣ ደብተር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ ማድረሱ ታውቋል።









Leave a Comment