0
#FastMereja I የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ” እየተጓዙ መሆናቸውን በአዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ገልጸዋል።
የአዲግራት ከተማ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ወታደሮቹ ከአዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

10 comments
ሃገሩ ነው ይግባ😊
Wow
🤔🤔መቀሌ ተቆጣጠርን ያሉትስ….. የት ደረሱ
ምን ችግር አለ ሀገራቸው ነው
ቀይባህር እንመልሳለን ስትሉ አባይን እዳታስወስዱት
ለድሮን ነው ይምጡ
ብልፅግና ጥሩ ጨዋታ ተጫውቷል። የሚቀጥለው የመከላከል እርምጃ loading
ይመቸው
ሰማዩም ምዱርም የኛ ነው ሲሉ አልነበር
ያኔ ገብተው የቀሩት ይሆናሉ
አብይ ሲጋብዛችው ችግር የለውም ከሱ ሲቃረኑ እንጂ አሁን እቺም ፖለቲካ መሆኗ ነው