banner

“HONOR” ስልክ በይፋ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱን አስታወቀ

#FastMereja I ዓለም አቀፍ የስማርት ስልኮች አምራች የሆነው ሆነር (HONOR) በይፋ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱን በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ባካሄደው መርሃ ግብር አስታወቀ።

በምረቃው ላይ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዲያ ተወካዮች እና የንግድ አጋሮች በተገኙበት፣ ኩባንያው የረጅም የባትሪ ህይወት፣ የላቀ የፎቶግራፊ ጥራት እና ዘመናዊ ዲዛይን ያላቸውን የቅርብ ጊዜ የስማርትፎን ፖርትፎሊዮዎቹን አስተዋውቋል።

የሆነር ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ለሚያደርገው የመስፋፋት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ሲሆን፣ ኩባንያው ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎች የላቁ የኤአይ (AI) ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ እና ከሀገር ውስጥ የንግድ አጋሮች ጋር ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጿል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment