banner

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ቤቶች ማህበር የስጋ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ አደረገ።

#FastMereja I የማህበሩ አመራሮች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ጋር ባደረጉት ቆይታ የማህበራቸውን ውሳኔ አሳውቀዋል።

የአዲስ አበባ ሉኳንዳ ቤቶች ማህበር አመራሮች በከተማዋ ከሚገኙ የስጋ ቤት ባለቤቶች ጋር ከተወያዩ በኋላ በአንድ ኪሎ የቁርጥ ስጋ ላይ የ500 ብር ቅናሽ አድርገዋል።

በውሳኔያቸው መሠረት በመዲናችን የሚገኙ ስጋ ቤቶች ከነገ 14/02/19 ዓ ም ጀምሮ አሁን ከሚሸጡበት የቁርጥ ስጋ ዋጋ 500 ብር ቀንሰው ለመሸጥ የወሰኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ማህበሩ ለንግድ ቢሮ በላከው ደብዳቤ 5000 ብር ይሸጥ የነበረ የቁርጥ ሰጋ 4500 ብር፣ 4500 የነበረ 4000 ብር እንዲሁም 4000 ብር ይሸጥ የነበረ የቁርጥ ስጋ 3500 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን አሳውቋል።

እንደ ማህበሩ አመራሮች ገለፃ ወደ ቤት ይዘው መሄድ ለሚፈልጉ ደንበኞች ለወጥና ለጥብስ የሚሆን ስጋ በትላልቅ ቁርጥ ቤቶች ለማህበረሰቡ በኪሎ 2500 ብር እስከ ጠዋቱ 4:00 ለመሸጥ መወሰናቸውንም አሳውቀዋል።

የማህበሩ ውሳኔ ከዚህ ቀደም ስጋን በዝቅተኛ ዋጋ ሲሸጡ የነበሩ ልኳንዳ ቤቶችንና የሸማች ህበረት ስራ ማህበራት ሱቆችን የማይመለከት መሆኑን አመራሮቹ አሳውቀዋል።

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ቤቶች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ወልደማርያም አባተ እንደገለፁት ማህበራቸው ከስጋ ተረፈ ምርት ጋር ተያይዞ ኤክስፖርት ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልፀው እነዚህ ስራዎች ሲሳኩ የስጋ ዋጋ ከዚህ በታች ይቀንሳል ብለዋል።

10 comments

Samuel Mekuanint October 23, 2026 - 3:02 pm

😂😂👍

Reply
Ibnu Nure Mohammed October 23, 2026 - 3:03 pm

ስለ ሽንኩርት አና ዳቦ እናዉራ እነዚህ ሙድ ዉስጥ ገብተዋል.

Reply
Banteamlak Tsega October 23, 2026 - 3:04 pm

የህዝቡ ጩኸት ነዉ ሚገርመኝ

Reply
Damene Bogale October 23, 2026 - 3:04 pm

ልዩነቱ ምንድነው?

Reply
Habtamu Astra Bizunesh October 23, 2026 - 3:04 pm

እንዴት ብዙ ቀንሰዋል ጭራሽ ለማባስ ነው የሚመስለው

Reply
Awake Ararso October 23, 2026 - 3:04 pm

ዮናስ ጨርጨር መጣሁልህ 🏃‍♂️🏃‍♂️

Reply
ንኩሉ ሰብ ሰላም October 23, 2026 - 3:04 pm

ቀልደኞች ናቹ እኮ ተዉን እባካቹ

Reply
Mastewal Eyasu October 23, 2026 - 3:05 pm

ኧረ ፎቶዬ 😭😭😭😭😭

Reply
MA Aklilu October 23, 2026 - 3:06 pm

ለሀብታሞች ድምፅ የሆናቹ እንኩዋን ደስ አላቹ

Reply
Simie Dida Hordofa October 23, 2026 - 3:06 pm

እያረፉ ይብሉት እኛ በዚህ የዝርፍያ ዋጋ ላለመብላት ወስኔናል‼️

Reply

Leave a Comment