banner

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡት ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑ እና ተማሪ ሙባረክ ሙሐመድ እውቅናና ሽልማት ተሰጠ

#FastMereja I በአማራ ክልል አስቸጋሪ ወቅቶች ተቋቁመው በ2018 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በክልል ደረጃ የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር አካሂዷል።

በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ በክልሉ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ሙባረክ ሙሐመድ (587 ያመጣ) እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሴቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑ (583 ያመጣች) የክልሉ መንግሥት ያዘጋጀውን ሽልማት ተረክበዋል።

ተማሪ ሙባረክ ሙሐመድ ስለተሰጠው እውቅና ሲናገር «የተበረከተልን ሽልማት ለወደፊቱ ትልቅ ኃላፊነት የጣለብን ነው» ያለ ሲሆን፤ በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ቆይታው በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን በመከታተል በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ሀገሩን ማገልገል እንደሚፈልግ ገልጻል።

በተመሳሳይ ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑ የተደረገላት እውቅና የሚያስደስትና ለቀጣይ ትምህርቷ የበለጠ የሚያበረታታት መሆኑን ገልጻለች። ሕዳሴ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ በመማር ለማኅበረሰቡ ችግር ፈጣሪ በሆኑ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ አስተዋጽኦ ለማበርከት ማቀዷን ተናግራለች።

በ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት 659 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 540 እና ከዚያ በላይ ያመጡ 193 ተማሪዎች የምስክር ወረቀት፣ የገንዘብ፣ የዋንጫ እና የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Comment